ባሕር ዳር: ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በርካታ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ በአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናት።
ባለፉት ዓመታት ደግሞ ከቀደምቶቹ የቱሪዝም መዳረሻዎች ባሻገር አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ተገንብተዋል። የቱሪዝም መነቃቃትም ተፈጥሯል።
ከዓመታት ወዲህ ግን ለቱሪዝም በተሰጠው ትኩረት የቱሪዝም ተጠቃሚነት እያደረገ መጥቷል።
በተለይም የክልሉ ሰላም መሻሻል በዘርፉ ላይ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ እና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች ወደ ክልሉ እንዲመጡ ዕድል ፈጥሯል ነው ያሉት።
በበጀት ዓመቱ ባለፉት ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ 16 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል። ከ152 ሺህ በላይ የሚኾኑ ዜጎች በዘርፉ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደኾኑም ገልጸዋል። ይህም የቱሪዝሙን መነቃቃት ያሳያል ነው ያሉት።
ይህ ተስፋ የተጣለበት የቱሪዝም ዘርፍ በአማራ ክልል መንግሥት የ25 ዓመት አሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።
በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም በማልማት ክልሉን ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ የማድረግ ግብ አንግቦ ወደ ሥራ ገብቷልም ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !









