በአፈ/ከሳሽ አገው ምድር እቁብ ማህበር በአፈ/ተከሳሾች እነ አለኸኝ አይናለም 5ቱ መካከል ባለው ገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአቶ ሽራው የኔሰው ቢተው የተመዘገበ እንጅባራ ከተማ 04 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መቅደስ ሽፈራው፣ በምዕራብ አለማየሁ፣ በሰሜን ገብሬ ሙላት እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሆነው መነሻ ዋጋ 1,790,226.00 /አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠና ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ስድስት ብር/ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከታህሳስ 07 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 07 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለ በኃላ ጥር 08 ቀን 2017 ዓ.ም 3፡00 እስከ 6:00 ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት