በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንክ ነገረ ፈጅ ሾፎኒያሽ ጎሹ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ እሚያምረው አስማረ በቁጥር 8 ሰዎች መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የ8ኛ አፈ/ተከሳሽ ንብረት የሆነውን በጋሸና ከተማ በምሥራቅ አማረ ፈንቴ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አድስ ሞላ እና በደቡብ መንገድ አዋሳኝ መካከል የሚገኘው ቤትና ቦታ በዜሮ መነሻ ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያው ከሀምሌ 08 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 07 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ነሀሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ ቤቱ ወይም ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በጋሸና ከተማ ቀበሌ 01 በመገኘት መግዛት ወይም መጫረት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ አሸናፊው የአሸነበትን ¼ ኛውን ወይም 25 በመቶ ለሃራጅ ባይ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡