ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

0
110

በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ ነገር ፈጅ ሶፎኒያስ ጎሹ እና በአፈ/ተከሣሾች  1ኛ ዋለ ተክሌ ፣2ኛ ይመር ተሾመ እና 3ኛ ተሾመ ወርቄ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በጉባላፍቶ ወረዳ 021 ቀበሌ ልዩ ቦታው ገብሬ አምባ በምሥራቅ አሌ ጌታቸው፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ጌታዋ በላይ እና በደቡብ ወርቁ ካሳው  ተዋስኖ የሚገኘው ንብረትነቱ የ2ኛ የአፈ/ተከሣሽ ይመር ተሾመ የሆነ ባለ አርባ ሁለት ዚንጎ ቆርቆሮ ክዳን ቤት በመነሻ ዋጋ 13,000.00 /አሥራ ሦሥት ሺህ ብር/ በሆነ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ለአንድ ወር አየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ በቀበሌው ማዕከል በመገኝት መጫረት  የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ¼ ኛው ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባይ ወዲያውኑ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here