በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙው የጃ/ወ/ት/ት/ጽ/ቤት አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ መጽሐፍቶችን በሐራጅ ጨረታ አውዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፍል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በጨረታው ማንኛውም ግለሰብ መሣተፍ ይችላል፣ እንዲሁም መጽሐፍ ያለበት መ/ብርሃን ከተማ ጃ/ወ/ት/ት ጽ/ቤት ሲሆን ጨረታው አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ መጋዘኑ ክፍት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰባት በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመሥሪያ ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አገልግሎት የማይሰጥ መጽሐፍ ሃራጅ ጨረታ ለአንድ ኪ.ግ መነሻ ዋጋ 7.00 /ሰባት ብር/ ሲሆን ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከ 16/07/2016 እስከ 30/07/2016 ዓ/ም ድረስ በአየር ላይ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ16/07/2016 እስከ 30/07/2016 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በቀን 01/08/2016 ዓ.ም በእለቱ በ8፡30 ታሽጎ 8፡45 ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም ካለም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ጊዜው ያለፈበትን መጽሐፍ ርክክብ የሚፈፀመው ያሽነፈበትን ጠቅላላ ብር ከገንዘብ ጽ/ቤት አካውንት ገቢ ሲያደረግ ወይም በተቋሙ መሂ/1 ገቢ ሲያደረግ ጃናሞራ ት/ት ጽ/ቤት መካነ-ብርሃን ከተማ የሚረከቡ ሲሆን ማንኛውም ወጭ በተጫራች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ለተከታታይ 40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁ. 058 294 00 23 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡