በአፈ/ከሣሾች 1ኛ ጌጡ ተሾመ፣ 2ኛ አስራቴ ካሳሁን ወኪል 1ኛ አፈጻፀም ከሳሽ እና በአፈ/ተከሣሽ ፀጋዓለም አዱኛው መካከል ስላለው የውርስ ንብረት አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በመቄት ወረዳ 02 ቀበሌ ልዩ ቦታው መቅርጫ በምሥራቅ የእግር መንገድ፣ በምዕራብ ወልዲያ/ወረታ መንገድ/፣ በሰሜን ፀጋ ስጦታው እና በደቡብ የእግር መንገድ ተዋስኖ የሚገኘው 477.5 ካ.ሜ ቦታ ላይ የሚገኝው 85 ዚንጎ ቆርቆሮ ቤት፣ 42 ዚንጎ አሞራ ክንፍ ቤት፣ ሰባት ዶርም ቤቶች እንዲሁም የውሃና የመብራት ቆጣሪ ጭምር ያለው ሲሆን በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ ስለዚህ የጨረታ ማስታወቂያው ከሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር በአየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ሀምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነምጨረታው በመቄት ወረዳ 02 ቀበሌ አስተዳደር ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን 25 በመቶ ወይም ¼ ኛውን ፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባይ ወዲያውኑ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡