ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
102

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. በቡሬ ከተማ ከሚገኘው መጋዝን ሎት 1. 10,000.00(አስር ሺህ ኩ/ል)፣ ሎት 2. 5,000.00(አምስት ሺህ ኩ/ል)፣ ሎት 3. 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ኩ/ል) ነጭ በቆሎ በሎት በመከፋፈል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንዬኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 8 የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ8ኛው ቀን 8፡00  ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ8ኛው ቀን 8፡30  ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም  ጨረታውን ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  7. ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሁለት በመቶ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ (ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማያያዝ አለበት)፡፡
  9. የማንሻ ወይም ሰብሉን አንስቶ የሚጨርስበት ጊዜ ለ5,000 ኩ/ል 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት፣ 10,000 ኩ/ል 30 ተከታታይ የሥራ ቀናት፣ 25,000 ኩ/ል 60 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒዬኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስጫኛ እና ሌሎች ወጭዎችን ገዥ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40/ 10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

 

የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here