ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
41

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ሁለ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ የ2017 ዓ.ም አዲስ ምርት ነጭ በቆሎ ሎት 1. 10,000 ኩ/ል ፣ሎት 2. 10,000 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ መሸጥ እና ሎት 3. ለዱቄት ፋብሪካ የሚውል የዶስፌር ማሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን  መስፈርት የሚያሟሉ  ተጫራቾች  መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉና እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የጨረታው ዋጋ ብር 200.000 /ከሁለት መቶ ሸህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/  በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1/ሂሳብ ክፍል/ እስከ መጨረሻው ቀን 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጄው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፣ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን  8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  6. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  10. የበቆሎ ማንሻ ጊዜ ለአንድ ሎት 20 ተከታታይ ቀናት ለሁለቱም ሎት ከሆነ 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለበት፡፡
  11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  13. የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 04 ቀበሌ ከሚገኘው መጋዝን ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ/ሁለ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here