ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
44

በአዊ አስተዳደር ዞን የሚገኘው አድማስ ሁለ/የገበ/የኀ/ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተ ለዩኒዬኑ ምርት እና ግብዓት ለማጓጓዝ አገልግሎት የሚውሉ 2 ሲኖትራክ ገልባጭ መኪኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. የጨረታ ዋጋው ከመገለጹ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ተሣታፊዎች የመሸጫ ዋጋውን በሠንጠረዥ በተገለፀው ዝርዝር ሁኔታ መሠረት መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው መሙላት አይችሉም፡፡
  6. በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚጀምረው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ወይም ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ የህዝብ በዓል ወይም የሥራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊው እንደታወቀ የአሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ለውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ5 ቀን ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጨረታ ማስከበሪያው 2 በመቶ ይወረስበታል፡፡
  9. ከጨረታው ጋር በተያያዘ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 77 91 22/09 98 01 27 00/ 058 227 16 81 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድማስ ሁለ/የገበ/የኀ/ሥራ ማኀበራት ዩኒየን ኃ/የተ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here