ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

የግዥ መለያ ቁጥር 20/2018 ዓ/ም

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሱታና ንግድና የማማክር ሥራዎች ኢትርፕራይዝ የፓስታ ማኮረኒ ለፋብሪካ ህንፃ ግንባታ ፕሮጅክት በሚቀርበው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጉልበት ሥራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ስነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ከፍለው ከሱታና ኢተርፕራይዝ ክፍል በመውሰድ በተያያዘው የሥራ ዝርዝር መሰረት የሚሰሩበትን ዋጋ በመሙላት በፖስታ አሽገው ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ኢተርፕራይዙ ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 203 ምትጫረቱበትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ16 ተኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋል፡፡ ቴክኒካል ዶክመንት በዕለቱ 4፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት  የሚከፈት ሲሆን የፋይናሻል ሰነድ የሚከፈትበት ቀን በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ (tax clearabce) ከግብር ስብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫረቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ መሰረት መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫረቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና ሙሉ ስም እንዲሁም አድራሻቸውን በመግለጽ በታሸገ ኢንቮሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫረቾች መወዳደር የሚችሉት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  7. በሎት 1 ተጫረቾች ደረጃ BC/GC-5 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
  8. ቴክኒካል እና ፋይናሻል ሰነዱ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  9. የሥራ መጠኑ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
  10. ጨረታ አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ከጠቅላላ ዋጋው 10 በመቶ የመልካም የሥራ አፈፃፀም ዋስትና (unconditnal bank guarantee) ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  11. ኢተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 42 26 44 ደዉለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here