በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ የእንስሳት መደሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 የእንስሳት መድሀኒት ግዥ እና ሎት 2 ቴትራ የእንስሳት መደሀኒት 3400 ሚ.ግ ፣3200 ቦክስ ሽያጭ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
 - የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 - የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅቦታል፡፡
 - ከላይ ከ1-3 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 8 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መሥሪያ ቤት /ሂሳብ ክፍል/ እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 - የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
 - የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
 - ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
 - የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ የእንስሳት መድኃኒት ግዥ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል የዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
 - አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡
 - ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 - በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
 - የማስረከብያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
 - ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
 
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ

