ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለገብ/ የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ. የትራክተር ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ቡስተር ኬሚካል መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 የፊት ጎማ ከነካላማዳሪው ብዛት 02 የኋላ ጎማ ከነካማዳሪው ብዛት 02 ፣ሎት 2 ኬሚካል ቡስተር ሸያጨ ብዛት 2600 ሊትር በጨረታ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ማጫረት  ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም፡-

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅቦታል፡፡
  4. ከላይ ከ1-3 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1 /ሂሳብ ክፍል/ እስከ መጨረሻው ቀን 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ተጫራች በሙሉ ዝርዝር ላይ በእያንዳንድ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
  7. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. የትራክተር ጎማ ግዥ አሸናፊው የሚለየው ጥቅል የዋጋ ድምር ነው፡፡
  11. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  14. የትራክተር ጎማ የማስረከብያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ሲሆን ቡስተር ኬሚካል የመረከቢያ ቡሬ የእርሻ ማእከል ሆኖ ማንሻ ቀን ብዛት 15 ቀን ይሆናል፡፡
  15. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት ሁለገብ/ የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here