የምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ከመደበኛ በጀት ለምግብ አገልግሎት የሚውል እህል እና የባልትና ዉጤቶችን አጫርቶ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን በሎት አንድ የምግብ እህል 1.ቀይ ጤፍ ፣2. በቆሎ ፣3. ነጭ ሌሌ ማሽላ ፣4. ጅሁላ ማሽላ እንዲሁም 5. ደበር ማሽላ በሎት ሁለት የባልትና ዉጤቶች ማለትም 1. የተዘጋጀ ሽሮ ፣2. የምግብ ዘይት ፣3. የምግብ ጨዉ ፣4. እርሾ ፣5. ጎመንዘር ፣6.ባቄላና አተር ክክ ፣7. በርበሬ እና 8. ፊኖ ዱቄት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ የሆነዉን አቅራቢ ድርጅት ለ9 ወር ከመስከረም 1 አስከ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ዉል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ /የቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የሚገዙ የእህል አይነትና የባልትና ዉጤቶች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእህል አይነትና የባልትና ዉጤት 1.5 በመቶ /በሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመሂ 1 ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ21/11/2017 እስከ 05/12/2017 ቀን ድረስ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉኃ ማረሚያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን በመቅረብ ከ1 እስከ 3 ያሉ ሰነዶችን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መዉሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ከ1 እስከ 3 ያሉት የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ከቆየ በኋላ በ16 ኛው ቀን ማለትም 06/12//2017 ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉኃ ማረምያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ስለሆነ ሁሉንም በሎት 1. የተቀመጠዉን የእህል ዋጋ እና በሎት 2. የተቀመጠዉ የባልትና ዋጋ ለየራሳቸዉ መሙላት አለባቸው፡፡ ካልተሟላ ግን ከጨረታ ወጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ የምግብ እህሉን እና የባልትና ዉጤቶች ምዕ/ጎ/ዞን ገ/ዉኃ ማረሚያ ቤት ንብረት ክፍል በዝርዝሩ መሰረት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ ዋጋ እንዲሁም የማይነበብ ሥርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ የምግብ እህል እና የባልትና ዉጤት አቅርቦት 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 327 03 39 በመደወል ጋዜጣ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ በምዕ/ጎ/ዞን ዐቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ እስከ 40 ቀን ድረስ ፀንቶ መይቆየት ይችላል
ምዕራብ ጎንደር ማረሚያ ቤት መምሪያ
ገ/ዉኃ