በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለጃ/ወ/መንገድ ትራንስፖትር ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ከደበላ ባርና ቀበሌ ያለውን 10.2 ኪ.ሜ መንገድ ለማሰራት አንድ ዶዘር ማሽን የሰሪት ዘመኑ እ.ኤ.አ ከ2009 ወዲህ የተመረተ ማሽን በሰዓት መከራየት ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም በተጫራች የሚሸፈን የዶዘር መጓጓዣ ሎቬድ ደረሶ መልስ፣ ናፍጣ፣ መለዋወጫ የሹፌር እና የረዳት አባል እንዲሁም ሌሎች አጠቃላይ ወጭዎች በተጫራች የሚሸፈን ሲሆን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ለተጨማሪ ሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዶዘር ማሽን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ ወይም ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከታህሳስ 20/2018 ዓ/ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከታህሳስ 20/2018 እስከ ጥር 10/2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 ጥር 12/2018 ዓ/ም 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት ፅንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የዶዘር ማሽን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ መንገድ ትራንስፖትር ጽ/ቤት ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

