በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በEU በጀት ለተሁለደሬ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 ማሽን /እስካቫተር/ እና የገልባጭ መኪና ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለው መነበብ መቻል አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አስራ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከ 3/10/2016 ዓ.ም እስከ 18/10/2016 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ18/10/2016 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል (ባይገኙም ይከፈታል)፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት /በድምር ዋጋ ነው/፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች መሥሪያ ቤቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግደታ አለበት፡፡
- ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ስራው ሳይጠናቀቅ ወይም እቃው ንብረት ክፍል ሳይገባ ቅድሚያ ክፍያ አይከፈልም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግሥት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡