ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
78

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን በአነደድ ወረዳ የአምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት በከተማ ዉስጥ ለዉስጥ ያለውን መንገድ ለማሰራት ይፈለጋል፡፡ ይህን መንገድ ለማሰራት የማሽነሪ ኪራይ ይፈለጋል ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረሩ ማሽነሪዎች ያላችሁ እንድትሳተፉ እናሳስባለን።

  1. ግሪደር
  2. ኤክስካቫተር
  3. ሩሎ
  4. ሻወር ትራክ፣
  5. ግልባጭ

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳድር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TI/ ያላቸው
  2. የኪራይ መጠን ከብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ስሌት ታክስ /VAT/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋርአያይዘው መቅረብ አለባቸው። ዝርዝር መግለጫ /specefication/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 /አራትመቶ ብር/ በመክፈል አምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 03ማግኘት ይቻላል።
  5. ተጫራቾች የጨራታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ማስያዝ አለባቸው
  6. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨራታ ሃሳባቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ፖስታ፤ ኮፒ የጨረታ ሃሳብ በአንድ ፖስታ በማድረግ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ አሽገው የድርጅቱን ሀጋዊ ማህተምና አድራሻውን በመሙላት ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በአነደድ ወረዳ በአምበር ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉና የጨረታ ሳጥን በዚሁ ዕለት 3፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ላይ በአነ/ወ/አ/ከ/መ/ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 የሚከፈት ሆኖ 21ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጫራታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል፡፡
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያሸነፉትን ንብረት ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን አነደድ ወረዳ አምበር ከተማ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡
  9. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት ውድድር) ነው፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ ከቀረበው አጠቃላይ የስራ መጠን/ዋጋ ላይ እስከ 20% መቀነስ እና መጨመር ይችላል፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በክፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጫራታው ዝርዝር መረጃ አምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582610012 እና 0582610712 በመደወል መረጃ መግኘት ይቻላል፡፡

    የአምበር ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here