ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
72

በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ /ሁለ/ህ/ስ/ማ/ ዩንዬን ኃ.የተ የ2017 ዓ.ም አዲስ ምርት ነጭ በቆሎ  ሎት1. ብዛት 5000 ኩ/ል፣ ሎት2. ብዛት 5000 ኩ/ል፣ ሎት3. ብዛት 5000 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን  መስፈርቾች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ / ብር በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ሂሳብ ክፍል እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻ ባሉበት ይከፈታል፡፡
  5. የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  9. የማንሻ ጊዜ ለ5000 ኩ/ል 15 ተከታታይ ቀናት በጥቅል ከሆነ 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለበት፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታ ማስታወቂያው ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 04 ቀበሌ ከሚገኘው መጋዝን ይሆናል፡፡
  13. መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40/1032 ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ /ሁለ/ህ/ስ/ማ/ ዩንዬን ኃ.የተ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here