በምዕ/ጐ/ ዞን /ዩ የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ ኒዬን ኃ.የተ የ5 ዓመት ስትራቴጅክ ፕላን ማስጠናት እና የስኳር ማጓጓዝ ትራንስፖርት ማጫረት ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም ሎት1. የአምስት አመት እስትራቴጅክ ፕላን ለማስጠናት፣ ሎት 2. የስኳር ማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ ከተጫራቾች ደረጃ አራት አጓጓዥ ድርጅት እና ከዚያ በላይ ማቅረብ እና ለአንድ አመት በየዙሩ ከሚመደብልን ቦታ ውል በመያዝ ለማጓጓዝ ፈቃደኛ መሆን ይገባቸዋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ስርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የዩንየኑን ዋና ዋና ተግባራት እና የስራ ዘርፎች ለቀጣይ አምስት አመት እቅድ መስራት የሚችል እና የጥናቱን መነሻ መረጃ ከስራ ክልሉ እና ከዩንየኑ ሙሉ መረጃ በየዘርፍ በመውሰድ መስራት የሚችሉ፡፡
- ለቀጣይ ዓመት እቅዱ በየአመቱ እየተሻሻለ ሊተገበር የሚችል እና የቀጣይ የገቢያውን ፣የአካባቢውን ፣ የሀገሪቱን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ተንትኖ በጥናት ላይ የተመሰረት ጥናት በማድረግ መስራት የሚችል፣ ሶስት እና ከዚያ በላይ የሰሩበት የተቋማት የስራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚሰበሰበው መረጃ የዳሞትን የስራ ክልል መሠረት ተደርጎ በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ መረጃ ማስባሰብ የሚችል መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፓስታ ውስጥ በማስገባት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በራስዎ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 8 የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ጫራቾች በተገኙበት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡ አሸናፊው የስኳር ማጓጓዝ በጥቅል ድምር ይሆናል።
- ተጫራቾች የጭነት ማዘጋጃና ዲስፓች ማዘጋጀት አለባቸው።
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0587740640 በመደወል ወይም
- በአካል በመገኘት መጠየቅ እና መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ ኒዬን ኃ.የተ