የጨረታ ቁጥር፡ EPSS/NCB/PS/11/2018
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባሕር ዳር ቅርንጫፍ አንድ ኮስትር ወይም ተመሳሳይ መኪና የመቀመጫ ወንበር ከ22-26 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ንፅህናውን የጠበቀ ተሸከርካሪ ባስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት ለሰራተኛ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአገልግሎት መ/ቤታችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለውድድሩ የሚያስፈልጉ መስፈረቶች
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቦርድ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከጥር 1/2018 እስከ ጥር 21/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ21 ኛው ቀን ጥር 21/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 3፡40 ባሕር ዳር ከተማ ጣና ሀይቅ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አገልግሎት መ/ቤታችን በአካል በመቅረብ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሰርቪስ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) 2 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ በአገልግሎት መ/ቤታችን የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የሰርቪስ አገልግሎት ማቅረቢያ ጊዜ ቢያንስ እስከ አንድ አመት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የአገልግሎት መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058 226 51 52 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት
ባሕር ዳር ቅርንጫፍ

