በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት1. የበቆሎ ሰብል ሽያጭ፣ ሎት2. ጤፍ ሰብል ሽያጭ፣ ሎት3. ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ፣ ሎት4. የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት5. የዱቄት ፋብሪካ የወለል፣ የጣሪያና የጎራንድዮ ጥገና የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአሽናፊው የሚሽጡትን መሽጥ እና የሚገዙትን መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው ሁኖ የግንባታ ሥራው ደረጃ ሰባት እና በላይ የሆነ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ዋጋው 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል/ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ እንዲታወቅ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት፣ ለሁለተኛ ጊዜ እና ለሦስተኛ ጊዜ የወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው 10 ተከታታይ የስራ ቀናት፣ ለሁለተኛ ጊዜ እና ለሦስተኛ ጊዜ የወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው በ10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ጊዜ የወጣው እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ቅዳሜ የዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
- የጨረታው አሽናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፍቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከአንድ ሎት ውስጥ ግን ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፤ ሎት3. ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ ሲሆን በስሩ የተከፋፈለ ሎት ስላለው በተከፋፈለው ሎት መሰረት መርጦ መሙላትም ሁሉንም መሙላት ይቻላል፡፡ ሎት4. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሲሆን ሎት1፣2 እና 5 ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ነው፡፡
- አሽናፊው የአሸነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊወስድ እና ሊያቀርብ ነው፡፡ ማንኛውም ወጭ አሸናፊው ይሸፍናል፤ የሚገዙትም ሆነ የሚሸጡት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡ አሽናፊው የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የአሸነፈበትን ግዥዎች በፍትህ ውሉ ከተመረመረ /ከተመዘገበ/ የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል ወይም ይሸፍናል፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 18 27 81 46/ 09 18 27 83 96 መጠየቅ ይቻላል፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.