ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
92

በአብክመ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.ሎት 1 የአፈረ ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ /የአገልግሎት ግዥ፣ ሎት 2 በቆሎ ሰብል ሽያጭ፣ ሎት 3 ያገለገሉ እቃዎች /ያገለገሉ ባዶ ጆንያ ሽያጭ እና ሎት 4 የፎሚጌሽን ሽራ ግዥ በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ  አወዳድሮ በአሽናፊው የምንከራየውን መከራየት የሚሸጡትን መሸጥ የሚገዛን መግዛት ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. በጋዜጣ የወጣው ግልጽ ጨረታ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነፃ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ  የሚከፈት ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ  የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ  ይከፈታል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሎት 1 ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ሎት 2፣3 እና 4 ናቸው፡፡
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡
  12. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከአንድ ሎት ውስጥ ግን ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡
  13. የአፈረ ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የመያዝ አቅሙ 30,000.00 ኩ/ል እና በላይ የሆነ ሲሆን የማከራየት ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  14. አሽናፊው የአሽነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሚሸጠውን ሊወስድ እና የሚገዛን ሊያቀርብ ነው፡፡ ማንኛውም ወጭ አሸናፊ የሸፍናል፡፡ የሚሸጡት ሆነ የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  15. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  16. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 27 81 46 /09 18 27 83 96 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here