በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1 የስኳር ማጓጓዝ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 2 ያገለገሉ ዕቃዎች /ባዶ ጆንያ/ ሽያጭ፣ ሎት 3 የሮለር ጥርስ ማስወጣት እና የፋብሪካ ዲናሞ ማስጠቅለል የአገልግሎት ግዥ በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የሚገዛዉን መግዛትና የሚሸጠዉን መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለስኳር ማጓጓዝ ለአንድ ዓመት ዉል ይዞ /ስኳር ማጓጓዝን ብቻ የሚመለከት/ የሚያጓጉዝ ሁኖ በየዙሩ (በየወሩ) 978 ኩ/ል 1ኛ.ከመትሃራ ስኳር ፋብሪካ ወደ ባ/ዳር ከተማ እና 2ኛ.ከአዲስ አበባ ወደ ባ/ዳር ከተማ ዉል በመያዝ ማጓጓዝ የሚችል ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ግልጽ ጨረታው ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞሉ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ በማስገባት ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 /ሶስት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ለመጀመሪያ ጊዜ በሎት 2 እና 3 ለወጣዉ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በሎት 1 ስኳር ማጓጓዝ ለወጣዉ ጨረታ ደግሞ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ወይም ወኪል ባይገኝም ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመር (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡ የሚጓጓዘውን አይነት መጠንና /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ይሆናል፡፡
- የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሸከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሁነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የስኳር የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የተሸከርካሪ ዝርዝር፣ የስሌዳ ቁጥር የመኪናው አይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርተት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ የታደሰ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በስኳር ማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ ተሳታፊ በመንገድ ላይ የሚከሰተውን ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡፡ የሚጓጓዘውን የስኳር መጠንና ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- የስኳር ማጓጓዝ ጊዜው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፣
- አሸናፊዉ የአሸነፈዉን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ያጓጉዛለል፣ ለሰራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛዉም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡፡
- ሁሉንም አይነት መሙላት ግዴታ ነዉ። ንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር በአንድ ሎት ዉስጥ ካለዉ፣
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 18 27 83 96 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.