ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ  

0
84

በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት1.ዩኒየኑ ከአቀፋቸው መሰረታዊ ህ/ስ/ማህበራት ወደ ዩኒየኑ መጋዝን ድረስ የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት የአገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ሎት2. የዱቄት ፋብሪካ መለዋወጫ ግዥ ፣ ሎት3.ፈርኒቸር ግዥ  ፣ሎት4.የመኪና ጎማና መለዋወጫ ግዥ ፣ ሎት5.የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ ፣ሎት6.የጽህፈት መሳሪያ ግዥ  ፣ሎት 7.የጽዳት እቃዎች ግዥ ፣ ሎት8.የአፈረ ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ ፣ ሎት9.የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ ፣ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ ደግሞ ሎት10. የሽንት ቤት ጥገና ግዥ፣ ሎት11. የአገለገሉት እቃ ሽያጭ ፣ሎት 12.የህትመት የአገልግሎት ግዥ  እና ሎት13. የኤሌክተሮኒክስ ግዥ  በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ አወዳድሮ ከአሽናፊው የሚጓጓዘውን ማጓጓዝ፣ የሚገዛውን መግዛት፣ የሚጠገነውን ማስጠገን እና የሚሸጠውን መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. በጋዜጣ የወጣው ግልጽ ጨረታ በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማየያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል/ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጡትን 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ የወጡትን ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላሉ፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  11. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10በመቶ (አስር በመቶ) በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  12. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ ወይም መርጦ መሙላት አይቻልም፡፡አሽናፊው የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ ያሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመር (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል ወይም ይሸፍናል፡፡
  13. የሰብል ማጓጓዝ ጊዜው እስከ ሀምሌ 30/2018 የሚቆይ ሲሆን ሰብል የመርክበ ኃላፊነት የዩኒየኑ ወይም የመሰረታዊ ህ/ስ/ማህበሩ የሚወክለው ንብረት ክፍል ሲሆን የማስጫኛና ማውረጃ ወጭ አሸናፊ ትራንስፖርተር አይከፍልም፡፡ የትራንስፖርት ማጓጓዣ ወጪ እና መንገድ ላይ የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች አሸናፊው ትራንስፖርት ይሸፍናል፡፡
  14. የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት ተጫራች በስማቸው የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  15. የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት የኪሎ ሜትር በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ከመነሻው እስከ ማራገፊያው ድረስ ያለው ኪሎ ሜትር ሲሞላ በትንሹም ቢሆን ሊቀንስና ሊጨምር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ቦታውን አውቃችሁ እንድትሞሉ፡፡ የሰብል ማጓጓዝ ትራንሰፓርት ጨረታ የሚፈለጉትን ማህበር መርጦ መሙላት ይቻላል ፡፡
  16. የአፈር ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለስድስት ወር የሚቆይ ሲሆን የማከራየት ፋቃድ ያለው መሆን አለበት የመያዝ አቅሙ ሀምሳ ሺህ እና በላይ የሆነ ሁኖ እንደ አስፈላጊነቱ የሚታራዘም ይሆናል፡፡ የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለአራት ወር የሚቆይ ሆኖ የመያዝ አቅሙ ሰላሳ ሺህና በላይ የሆነ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፡፡የመጋዝን ኪራይ አሸናፊ የሚለየው በአንድ ኩንታል ዋጋ ሲሆን ዋጋው የሚሞላው የአንድ ኩ/ል ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ ይሞላ ምክንያቱም አሸናፊው የሚለየው ርዝመት ቁመት ወርድ-15%/1.8*10= መጋዝን የመያዝ አቅም ስለሚሰጥ የተሞላው የብር መጠን ሲካፈል መጋዝኑ የሚይዘው የኩ/ል መጠን በማድረግ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን የመጋዝኑ የመያዝ አቅሙ ዩኒየኑ በሚያዋቅረው ኮሜቴ ተለክቶ በሚገኘው መሰረት ይሆናል፡፡የምንከራየው የመጋዝን ኪራይ ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሁኖ አሸናፊውን በቅድም ተከተል የሚያዝ ይሆናል፡፡
  17. አሽናፊው የአሽነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ሊያቀርብ ነው፡፡ ለስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ የሸፍናል፡፡የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛሉ፡፡
  18. ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ በተገለጸው ሎት 11 ከሀ-ሐ ስር ከጨረታ ሰነዱ ላይ በሚዘረዘረው መሰረት መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡
  19. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  20. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 10 63 46 46 / 09 11 59 05 34/ መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here