የላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 ዓ.ም በጀት አመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ምድብ1 ፡ የጽህፈት መሳሪያዎች ምድብ 2 ፡ የጽዳት ዕቃዎች ምድብ 3 ፡ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት በሚከተሉት ዝርዝር መስፈርቶች መሰረት መጫረት ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቲን ያላቸው፡፡
- የሚያቀርቡት እቃ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳታፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚያቀርቡት እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (እሰፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለሥ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይኖርባቸዋል፡፡ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት እቃ 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ እና በጥሬ ገንዘብ /በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያበጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባትይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይዘጋና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊወኪሎቻቸውበ16ኛው ቀን በ4፡00 በተገኙበት ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ ይስተጓጐልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሽነፉትን እቃዎች በየፑሉ ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ዋጋ ነው፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ከሎቱ ውስጥ ያንዱን ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- .ጨረታው ለ40 /አርባ/ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሥለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ቢሮ ቁጥር 4 ድረሰ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058-445-1399/ 058-445-0005 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

