ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስማቸው ከዚህ በታች የተጠቀሱት ተበዳሪዎች ያለባቸውን ብድር በወቅቱ ባለመክፈላቸው ምክንያት ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 626/2001 እና በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለብድሩ በዋስትናነት ወይም በመያዣነት የተያዘውን የመኖሪያ ቤት በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዥ ስም | የንብረቱ ዓይነት | የቤቱ/የቦታው/ ስፋት | የሐራጅ መነሻ
ዋጋ |
ሃራጅ የሚካሄድበት
ቦታ |
ዱርቤቴ ቅርንጫፍ | አቶ ታዘበው አቤ ዓለሙ እና አቶ እንዳለው ፈንታሁን ውቤ | አቶ ሙሉሀብት ገብሬ መንጌ | የመኖሪያ ቤትና ቦታ | 200 ካ.ሜ | 1,774,488.26 | በመኖሪያ ቤቱ
ነሀሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 5፡00 |
ማሳሰቢያ፡-
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪል የሐራጁን መነሻ ዋጋ 5 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በማስያዝ መጫረት ይችላል፣
- አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈለ ለሐራጅ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም፣
- ሐራጁ የሚካሔድበት በአማራ ክልል በሰ/ጎጃም ዞን ዱርቤቴ ከተማ 01 ቀበሌ በመኖሪያ ቤቱ፤
- በጨረታው ላይ ተጫራቾችና ባለንብረቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡
- ተቋሙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በመንግሥት የሚፈለጉ ግብሮችን፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታው አሸናፊ ይሸፍናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-582-230-783 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ