ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስሙ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ተበዳሪዎች ያለባቸውን ብድር በወቅቱ ባለመክፈላቸው ምክንያት ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 626/2001 እና በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለብድሩ በዋስትናነት ወይም በማያዣነት የተያዘውን የመኖሪያ ቤት በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዥ ስም | የንብረቱ ዓይነት | የቤቱ ሥፋት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ | ሃራጅ የሚካሄድበት ቦታ |
ወረታ ቅርንጫፍ
|
ወ/ሮ ዉብ ማረዉ | ወ/ሮ ዉብየ ማረዉ | የመኖሪያ ቤትና ቦታ
|
148.5 ካ.ሜ | 710,850.00 | ጣና ማ/ፋ/ተቋም በወረታ ቅርንጫፍ ጥር 14, 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 5፡00 |
ማሳሰቢያ፡–
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪል የሐራጁን መነሻ ዋጋ አምስት በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈለ ለሐራጅ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡
- ሐራጁ የሚካሔድበት ቦታ በአማራ ክልል ደ/ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ 03 ቀበሌ በቅርንጫፉ ጽ/ቤት ነው፡፡
- በጨረታው ላይ ተጫራቾችና ባለንብረቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡
- ተቋሙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በመንግስት የሚፈለጉ ግብሮችን እና የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታው አሸናፊ ይሸፍናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 251 584 461 814 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ