የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ እስክ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያና ንግድ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 300 ብር በመክፈል ሞጣ ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በስራ ስዓት እስከ ቀኑ 11፡ 00 ስዓት ብቻ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ኘሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 3፡00 በከተማ አስተዳደሩ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ10በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ሰነድ ከዋጋ እና ከሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ 0586612040/ 0586610027 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት