ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሰብል ሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
155

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. በቡሬ ከተማ ከሚገኘው መጋዝን ሎት 1. 10,000 (አስር ሸህ) እና ሎት 2. 7,126.6 (ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ስድስት ነጥብ ስድስት) ኩ/ል ነጭ በቆሎ በሎት በመከፋፈል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም፡-

  1. በጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
  2. ማንኛውም ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም::
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፓስታ ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለባቸው::
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኒ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ::
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 11 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ11ኛው ቀን 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል:: ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም::
  7. ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፈቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት:: ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሁለት በመቶ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል::
  8. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት:: (ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማያያዝ አለበት)::
  9. የማንሻ ወይም ሰብሉን አንስቶ የሚጨርስበት ጊዜ 10,000 ኩ/ል 30 ተከታታይ የሥራ ቀናት እና 7,126.6 ኩ/ል 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት  ይሆናል::
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገዱ ይሆናሉ::
  12. የማስጫኛ እና ሌሎች ወጭዎችን ገዥ የሚሽፍን ይሆናል::
  13. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40/ 10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ::
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here