ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
100

በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.ሎት 1 ሰብል 83,150.00 /ሰማንያ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ/ ኩ/ል ዩኒየኑ ካቀፋቸው መሰረታዊ ማህበራት ወደ መርከብ ሁ/የገ/ህስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተ.መጋዝን የማጓጓዝ የትራንስፖርት (የአገልግሎት) ግዥ በግልጽ በጋዜጣ  ጨረታ በማውጣትና በማወዳደር በአሽናፊው የሚጓጓዘውን ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ በማስገባት ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. በጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡ የሚጓጓዘውን አይነት መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ይሆናል፡፡
  12. ሰብል ማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሸከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሁነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  13. ሰብል ማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የተሸከርካሪ ዝርዝር ፣የስሌዳ ቁጥር የመኪናው አይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ የታደሰ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  14. ሰብል ማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ ተሳታፊ በመንገድ ላይ የሚከሰተውን ማንኛውም ወጭ አሸናፊ የሸፍናል፡፡ የሚጓጓዘውን የሰብል አይነት መጠንና ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡ ሲፒኦ ሲያሲይዙ ሁለት የማራገፊያ ጣቢያ ስላለ ሩቅ በሆነው ጣቢያ ታስቦ ሲፒኦ መያዝ አለበት፡፡
  15. የሰብል ማጓጓዝ ጊዜው እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  16. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  17. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 18 27 83 96 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here