ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ የእንስሳት መደሃኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም  ተጫራቾች የሚከተሉትን  መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅቦታል፡፡
  4. ከላይ ከ1-3 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ በመቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መሥሪያ ቤት /ሂሳብ ክፍል/ እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጄው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  6. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here