በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. ስንዴ 2500 /ሁለት ሽህ አምስት መቶ/ኩ/ል እንጅባራ ከተማ ከሚገኘዉ ከአድማስ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ/የተ. ወደ ባ/ዳር ከተማ ዩኒየኑ መጋዝን የማጓጓዝ የትራንስፖርት (የአገልግሎት) ግዥ በግልጽ አወዳድሮ ዉል በመያዝ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ያላቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒዩ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ዋጋ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒዩ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ በማስገባት ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮቁጥር 101 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታው አሽናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል/ ይሸፍናል፡፡የሚጓጓዘውን አይነት መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ይሆናል፡፡
- ስንዴ ማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሸከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሁነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ስንዴማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የተሸከርካሪ ዝርዝር ፣ የስሌዳ ቁጥር የመኪናው አይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ የታደሰ ምዝገባ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ስንዴ ማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ ተሳታፊ በመንገድ ላይ የሚከሰተውን ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡የሚጓጓዘውን የሰንዴ አይነት መጠንና የርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- የስንዴ ማጓጓዝ ጊዜው ዉል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ዉስጥ አጠቃሎ ማስረከብ አለበት ፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34/ 09 18 27 83 96/09 18 01 22 02 መጠየቅ ይቻላል፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.