በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት ሁለገብ/ የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ. የትራክተር ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ቡስተር ኬሚካል መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 የፊት ጎማ ከነካላማዳሪው ብዛት 02 የኋላ ጎማ ከነካማዳሪው ብዛት 02 እና ሎት 2 ኬሚካል ቡስተር ብዛት 2600 ሊትር በጨረታ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም፡-
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- ከላይ ከ1-3 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሂሳብ ክፍል እስከ መጨረሻው ቀን 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ተጫራች በሙሉ ዝርዝር ላይ በእያንዳንዱ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የትራክተር ጎማ ግዥ አሸናፊው የሚለየው በጥቅል የዋጋ ድምር ነው፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- የትራክተር ጎማ የማስረከብያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ሲሆን ቡስተር ኬሚካል የመረከቢያ ቡሬ የእርሻ ማእከል ሆኖ ማንሻ ቀን ብዛት 15 ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት ሁለገብ/ የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ.