ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
108

በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት1. 30,000 ኩ/ል እና በላይ የመያዝ አቅም ያለዉ የሰብል ማከማቻ መጋዘን ኪራይ መከራየት አገልግሎት ግዥ፣ ሎት፣ 2 የሮለር ጥርስ ማስወጣት፣ ሎት. 3 የፋብሪካ ዲናሞ ማስጠቅለል  የአገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዉል በመያዝ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፤ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin No/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማየያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል/ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ በማስገባት ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨርታ ሰነዱን ማስታቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣዉ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ተወዳዳሪዎች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ  የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. አሽናፊው የሚለየው በተናጥል ሲሆን የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመር (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል/ይሸፍናል፡፡
  12. አሸናፊው ዋጋ ሲሞላ የአንድ ኩ/ል ዋጋ ታሳቢ አድርጎ ይሙላ፡፡ምክንያቱም አሸናፊ የሚለየው ርዝመት፣ቁመት፣ወርድ-15%/1.810 = መጋዝኑ የሚያዝ አቅም ስለሚሰጠን የተሞላውን የብር መጠን ሲካፈል መጋዝኑ የሚይዘው የኩ/ል መጠን በማድረግ አሸናፊ የሚለይ መሆኑ ይታወቅ፡፡
  13. የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የመያዝ አቅሙ 30,000.00 እና በላይ የሆነ ሲሆን መጋዝን የማከራየት ፍቃድ ያላቸው ወይም መጋዝን ለማከራየት ፍቃደኛ የሆኑ ሁነው ካርታና ፕላን ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማያያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡ መጋዝኑ ያረፈበት ቦታ ተሳቢ መኪና የሚያዘዋውርና ስፋት ያለው መሆን አለበት፡፡
  14. ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡ ለይቶ መሙላት አይቻልም ሁሉንም አይነት መሙላት ግዴታ ነዉ ማለትም ንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር በአንድ ሎት ዉስጥ ካለዉ ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34 /09 18 082626 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here