ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

የዳሞት የገ/ሁለ/ህ/ስ/ማ/ ዩኔዬን ኃ.የተ Gt5 ህንጻ የሚያስፈልጉ እቃዎችን ሎት 1 ፈርኒቸር እቃዎች ከነመገጣጠሚያው ፣ሎት 2 የመጋረጃ ቁሳቁስ ከነእጁ ፣ሎት 3 የሳውንድ ሲስተም እስከመገጣጠሚያው ፣ሎት 4 ላይትቦክስ /ዲጅታል ታፔላ/ እስከ መገጣጠሚያው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቾች የሚያሟሉ  ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸዉና እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የጨረታው ዋጋ ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ሸህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1 /ሂሳብ ክፍል/ እስከ መጨረሻው ቀን 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው  ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን  8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  6. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን አለበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 03 ቀበሌ ከሚገኘው ዋና ቢሮ ነው፡፡
  13. .ተጫራቾች ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ/ሁለ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here