በአብክመ በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሉማሜ ከተማ አሰተዳደር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የተለያዩ የውሃ እቃዎችን፣ ቆጣሪ፣ የቧንቧና መገጣጠሚያ፣ ህትመት፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች /እስቴሽነሪ/ እና ኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የዘመነ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከሚገዙት የጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ በገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 18/02/2017 ዓ.ም እስከ 03/03/2017 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 በቀን 03/03/2017 ዓ.ም በ3፡00 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል መገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 772 04 65 /06 45 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
መሥሪያ ቤቱ የጨረታውን ሃያ አምስት በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ከተጫራቾች ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር /with hold tax/ ሁለት በመቶ ከግዥው ዋጋ ላይ የሚቀነስ ይሆናል፡፡
አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ውል መያዝ አለበት፡፡
አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
አሸናፊው ያሸነፈውን እቃ ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
አሸናፊው የሚለየው በሎት ነው፡፡
የሉማሜ ከተማ አስተዳደር መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት