የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ህጋዊና ብቃት ካላቸው በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ማለትም፡- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ፣ ሎት 4 የመኪና ሽቶዎችና ተዛማጅ እቃዎች እና ሎት 5 የመኪና የወንበር ልብስ ሥራ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት አድራሻው ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 05 /የገቢዎችና ጉምሩክ ቢሮ የነበረዉ/ ባለዉ G+4 ህንፃ ላይ ቢሮ ቁጥር 412 በመምጣት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው::
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
3. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ::
5. ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን የሚረከበው በተጠቃሚዎች የጥራት ትክክለኛነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው::
6. አሸናፊው ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ የዉል አፈጻጸም ዋስትና /ፐርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::
7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱም ሆነ ከተጠየቀዉ ስፔስፊኬሽን ዉጭ ምንም አይነት ጽሁፍ ማስፈር የለባቸውም::
8. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም::
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 304 ከረፋዱ 4፡15 በግልጽ ይከፈታል:: 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል::
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
11. ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 00 82 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት