ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ  ግልፅ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
75

የመቀጠዋ ወረዳ/ገ/ ጽ/ቤት ለመቀጠዋ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ለውልሃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንግስት መደበኛ በጀት ባለ አንድ ብሎክ ባለ አራት የመማሪያ ክፍል በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ  መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፣ከደረጃ 7 በላይ የሆኑ፡፡
  1. የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሠጥ እንደተጫራቹ ምርጫ (ሲ.ፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ መሂ-1 ገቢ ሆኖ የጠቅላላ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሠረት በማድረግ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ  መጠን ተወስኖ በጨረታ ጥሪው እና ሰነዱ ውስጥ መገለፅ ይኖርበታል፡፡ ይህም በመቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  2. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል
  3. ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ተግባራት ባለመፈፀሙ ምክንያት ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሙሉ በግዥ ፈጻሚው አካል ሊወረስበት ይችላል፡፡ 1ኛ. በጨረታ ሠነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሠነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ተጫራቹ ራሱን ከጨረታው ካገለለ፡፡ 2ኛ.በጨረታው ውድድር አሸናፊ በመሆኑ የውል ማስከበሪያ እንዲያስዝ እና ውል እንዲፈረም ተጠይቆ የውል ማስከበሪያውን ለማስያዝ ፍቃደኛ ካልሆነ፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ ማሸነፋ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ በዚህ ውስጥ በተካተቱ የዋስትና ዓይነቶች የሞሉን ዋጋ 10 በመቶ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች (ሲ.ፒኦ) ወይም በገንዘብ ያዥ መቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመሂ-1 በጥሬ ገንዘብ  ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  5. በግዠው አፈጻጸም ላይ አቤቱታ ቀርቦ በማጣራት ላይ ካልሆነ በስተቀር አሸናፊው ተጫራቹ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ ያላስያዘ እና ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ግዥ ፈጻሚው አካል የጨረታ ማስከበሪያ የመውረስ መብት አለው፡፡
  6. ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያ የመድን ዋስትና አገልግሎት የማንቀበል መሆኑ ይታወቅ፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ እና ስርዝ ድልዝ ካለዉ ከጨረታ ዉጪ ይሆናሉ፡፡
  8. ቅድሚያ ክፍያ ወይም 30በመቶ የማንከፍል  መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ አሸናፊ ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ ማስከበሪያ የሠነድ ሽያጭ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ሰነዱን ገዝቶ የገዛበትን ሠነድ ኮፒ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
  13. የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን ያልገዛ እና የገዛበትን ሠነድ ኮፒ ያላስያዘ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ እንደሚሆን አውቆ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  14. ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ  በ22ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 430 ላይ ይከፈታል፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል እና ኮፒውን በመቀጠዋ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት/ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ዞን ግብርና መምሪያ ጊዜዊ ቢሮ   ማቅረብ አለበት፡
  16.  እኩል የወጡት ተጫራቾች መሆናቸው ሲረጋገጥ ተገልጾላቸው መጀመሪያ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለጹት መስፈርቶች መሠረት የመጨረሻ የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡ የሚጠየቅ መሆኑን እና እኩል የወጡት ተጫራቾች ያቀረቡት የመጨረሻ መወዳደሪያ ሀሳብ ተገምግሞ የተሻለ ሀሳብ ያቀረበው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ተደርጎ ይመረጣል ፣በመጨረሻው ውድድር እኩል ከወጡት ተጫራቾች መካከል ሴቶች ካሉ ቅድሚያ ለሴቶች ይሠጣል፡፡
  17. ተጫራቾች ዋጋ በሚሞሉበት ሰነድ ላይ ሙሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  18. ስለጨረታዉ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይችላሉ፡፡
  19.  ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዞን ግብርና መምሪያ ጊዜዊ ቢሮ በመምጣት መቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የመቀጠዋ ወረዳ/ገ/ ጽ/ቤት

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here