ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ የተለያዩ ጨረታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ሎት1. ሰብል ማጓጓዝ በመሠ/ማህበራት ያለውን ሰብል ወደ ቡሬና ደምበጫ ከተማ ወደተለያዩ መጋዝኖች ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ተጫራቾች የኤፌሳርና ከዚያ በላይ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ሎት2. የጽዳትና የጽህፈት መሳሪያወች ግዥ ፣ሎት3. ሶፍትዌሮችን ጅፒኤስ ግዥ፣ ሎት4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ ሎት5. የኤሌክትሮኒክስና ተዛማች ዕቃዎች ግዥ ፣ሎት6. የተለያዩ አልባሳት ግዥ፣ሎት7. ህትመት ግዥ፣ ሎት8. የአትክልት ዘር ቀይ ስርና ካሮት ሽያጭ፣ሎት9. የፋብሪካ  መለዋወጫ  እቃዎች ግዥ ሎት10. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ፣ሎት11. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ግዥ፣ ሎት12.  የሰብል መደርደሪያ ፓሌት ግዥ ብዛት 100፣ ሎት13. መጋረጃ ቁሳቁስ ከነእጁ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  3. የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ወይም ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ሁለት በመቶ ሲሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ወይም በጥሬ ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታው ዋጋ 200.000 (ከሁለት መቶ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኑ ሂሳብ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቀረቢያ ሰነድ ላይ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በፓስታው ውስጥ ማስገባት እና ፓስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ከላይ በተገለፀው አግባብ የመጫረቻ ሠነዳቸውን በማዘጋጀት ማስታወቅያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆን እና በአስረኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በሚቀጥለው ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  10. የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም ጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  11. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ድምር 10በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  1.  የሰብል ማጓጓዝ ተጫራቹ በራሱ ስም የተዘጋጀ የማጓጓዣ ሰነድ/ዲስፓች/ ማዘጋጀት አለበት፡፡
  2. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  3. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  4. ለሰብል ማጓጓዝ ማንኛውም ተጫራች የቀረፅ እና ሌሎች ወጭዎችን መሸፈን አለባቸው፡፡
  5. ለሰብል ማጓጓዝ ማንኛውም ተጫራች ሁሉንም ጣቢያዎች የመሙላት ግዴታ አለበት፡፡
  6. ለሰብል ማጓጓዝ አሸናፊ የሚለየው በየጣቢያው ዝቅተኛ ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡
  7. ሌሎች ጨረታዎች አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  8.  ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 774 640 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here