ለመጀመሪያ ፣ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
62

በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት1.የዶቄት ፋብሪካ መለዋወጫ ግዥ ለሶለተኛ ጊዜ፣ ሎት2.የመኪና ጎማና መለዋወጫ ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ፣ ሎት3.የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ፣ ሎት4.የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ ፣ሎት5.የጽዳት እቃዎች ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ፣ ሎት6.የህትመት የአገልግሎት ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ ሎት7.ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ለሶሰተኛ ጊዜ፣ ሎት 8.ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነ መጋዘን ለማሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት9፣ የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ ለሶሰተኛ ጊዜ እና ሎት11. የሰብል ማጓጓዝ ትራንሰፓርት ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ አወዳድሮ ከአሸናፊው የሚጓጓዘውን ማጓጓዝ፣ የሚገዛውን መግዛት፣ የሚሰራውን ማስራት እና የሚሸጠውን መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒዩ ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨርታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጡትን 10 ተከታታይ የሰራ ቀናት ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ የወጡትን ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁለተኛና ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው 7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ  የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ፤በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡ለመጀመሪያ ለወጣው 10 ተከታታይ የሰራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ  የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡አሽናፊው የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመር (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ ይምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል ወይም ይሸፍናል፡፡ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ከሀ-ሐ ድረስ ከተዘርዘሩት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንዱ ፊደል ሎት ካለው ቀንሶ መሙላት አይቻልም ፡፡
  12. የሰብል ማጓጓዝ የመረከብ ኃላፊነት የዩኒየኑ ወይም የመሰረታዊ ህ/ስ/ማህበሩ የሚወክለው ንብረት ክፍል ሲሆን የማስጫኛና ማውረጃ ወጭ አሸናፊ ትራንስፖርት አይከፍልም፡፡የትራንስፖርት ማጓጓዣ ወጪ እና መንገድ ላይ የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች አሸናፊው ይሸፍናል፡፡
  13. የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት የኪሎ ሜትር በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ከመነሻው እስከ ማራገፊያው ድርስ ያለው ኪሎ ሜትር ሲሞላ በትንሹም ቢሆን ሊቀንስና ሊጨምር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ቦታውን አውቃችሁ እንድትሞሉ፡፡ የሰብል ማጓጓዝ ትራንሰፓርት ጨረታ የሚፈለጉትን ማህበር መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡
  14. የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለአራት ወር የሚቆይ ሁኖ የመያዝ አቅሙ ሰላሳ ሺህና በላይ የሆነ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፡፡የመጋዝን ኪራይ አሸናፊ የሚለየው በአንድ ኩንታል ዋጋ ሲሆን ዋጋ የሚሞላው የአንድ ኩ/ል ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ ይሞላ ምክንያቱም አሸናፊ የሚለየው ርዝመት*ቁመት*ወርድ 15በመቶ ወይም 1.8*10=መጋዝን የመያዝ አቅም ስለሚሰጥ የተሞላው የብር መጠን ሲካፈል መጋዝኑ የሚይዘው የኩ/ል መጠን በማድረግ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን የመጋዝኑ የመያዝ አቅሙ ዩኒየኑ በሚያዋቅረው ኮሜቴ ተለክቶ በሚገኘው መሰረት ይሆናል፡፡የምንከራየው የመጋዝን ኪራይ ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሁኖ አሸናፊውን በቅድም ተከተል የሚያዝ ይሆናል፡፡
  15. አሽናፊው ያሸነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ሊያቀርብ ነው፡፡ለስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  16. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  17. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34/09 18 082626 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here