ለመጀመሪ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ ነጭ በቆሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 ነጭ በቆሎ የ2017 ዓ.ም አዲስ ምርት ብዛት 10,000 ኩ/ል እና ሎት 2 የከረመ ነጭ በቆሎ ብዛት 14,586 ኩ/ል የሚጫረቱ  ተጫራቾች የሚከተሉትን  መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. ከላይ ከ1-2 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት /ሂሳብ ክፍል/ እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣ ጫረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  5. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  9. የማንሻ ጊዜ 1ኛ የ2017 ዓ.ም አዲስ ምርት ለነጭ በቆሎ 25 ቀን 2ኛ የከረመ ነጭ በቆሎ 35 ቀን ማንሳት አለበት፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 04 ቀበሌ ከሚገኘው መጋዝን ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here