ለመጀመሪ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
65

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ሁለ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ የ2017 ዓ.ም አዲስ ምርት ነጭ በቆሎ በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 ብዛት 5000 ኩ/ል ፣ሎት 2 ብዛት 5000 ኩ/ል እንዲሁም ሎት 3 ብዛት 5000 ኩ/ል የሚጫረቱ  ተጫራቾች የሚከተሉትን  መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ሂሳብ ክፍል እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጄው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  5. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  9. የማንሻ ጊዜ ለ5000 ኩ/ል 15 ተከታታይ ቀናት በጥቅል ከሆነ 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለበት፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 04 ቀበሌ ከሚገኘው መጋዝን ይሆናል፡፡
  13. .ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here