ለመጅመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ፣

0
84

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሉማሜ ከተማ አስተዳደር የሉማሜ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የ5 ዓመት ኦዲት ለማስደረግ በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ አወዳድሮ ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የቫት ተመዝጋቢየሆኑ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫራቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጁዎች ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ በገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ08/07/2017 ዓ.ም እስከ 23/07/2017 ዓ.ም እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 በቀን 23/07/2017 ዓ.ም በ 3፡00 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል መገኘት ወይም በ 058 772 06 45 /06 45 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ ሃያ አምስት በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጫራቾች ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር /with hold tax/ ከግዥው ዋጋ ላይ የሚቀነስ ይሆናል፡፡
  15. አሸናፊው ማሸነፉ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ውል መያዝ አለበት፡፡
  16. አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  17. አሸናፊው የሚለየው በሎት ነው፡፡

የሉማሜ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here