በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 በጀት አመት ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች አገልግሎት የሚዉል የመኪና የጭነት ኪራይ ባሕር ዳር ደርሶ መልስ ኦክስጅን ሲሊንደር አስሞልቶ ጭኖ ለማምጣት እና መድሐኒት ከጎንደር ወደ መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማጓጓዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር የከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመኪናውን ሊቭሪ (የባለቤትነት ማረጋገጫ) ፎቶ ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ
- ለጨረታ የሚቀርበው ተሸከርካሪ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት የሚውል መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ኦክስጅን ሲሊንደር ያልተሞላውን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ጭኖ ባሕር ዳር ኦክስጅን ማምረቻ አስሞልቶ መተማ ሆስፒታል ማምጣት የሚችሉ፤
- የመድን ኢንሹራንስ ውል ያላቸው እና ኮፒውን ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ስዓት በመተማ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በስራ ሰዓት ጨረታውን ከህዳር 15/2018 እስከ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16 ኛው ቀን ማለትም በ ህዳር 30/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና በሰነዱ ላይ ስም እና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጭነት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም (ሲፒኦ) ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጭነቱ አይነት በቢያጆ ሲሆን በምዕ ጎ/ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ እንዲጫን በሚጠየቅበት ሰዓት በአስቸኳይ ማምጣት የሚችል መሆንአለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 01 74 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-ኦክስጅን ሲሊንደር ከመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ባሕር ዳር ጭኖ አስሞልቶ ለማምጣት በሚሔደበት ቀን በመብራት መጥፋት ምክኒያት ወይም በወረፋ ምክኒያት ቢዘገይ ወረፋውን ጠብቆ አስሞልቶ መምጣት የሚችል፡፡
የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል

