የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ከወረቀት ነጻ የሆነ ህክምና ለመስጠጥ የፉል አዉቶ ሚሽን (ሙሉ ኔትወርኪግ) ሶፍት ዊር ለመግዛት ሶፍት ዊር አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የአንድ ጊዜ የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከታወቀ ሆስፒታል ላይ የፉል አዉቶሜሽን ስራ ለመስራታቸዉ እና ከ1 ዓመት በላይ ለመስራቱ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ሶፍትዌር አቅራቢዎች ሶፍት ዌር ለመፍጠራቸዉ የባለቤትነት መብት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ አሸናፊዉ ክፍያ የሚከፈለዉ ሥራውን ሰርቶ ካጠናቀቀ እና ሥራዉ በባለሞያ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ግዥዎች ለአንድም ግዥ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመሄድ ለሁሉም ሎቶች የመጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በብር 100 (አንድ መቶ ብር) ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና አገልግሎት ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ 20 በመቶ ከግዥዉ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 00 16 /00 63 /10 16 በመደወል ወይም ፋክስ ቁጥር 058 775 13 32 መላክ ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

