ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
99

በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ የ5 ዓመት ስትራቴጅክ ፕላን ማስጠናት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የአምሰት ዓመት እስትራቴጅክ ፕላን ለማስጠናት በግልጽ ጨረታ አውጥቶ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የዩንየኑን ዋና ዋና ተግባራት እና የሥራ ዘርፎች ለቀጣይ አምስት አመት እቅድ መስራት የሚችል እና የጥናቱን መነሻ መረጃ ከሥራ ክልሉ እና ከዩንየኑ ሙሉ መረጃ በየዘርፉ በመውሰድ መስራት የሚችል፡፡
  4. ለቀጣይ ዓመት እቅዱ በየአመቱ እየተሻሻለ ሊተገበር የሚችል እና የቀጣይ የገቢያውን የአካባቢውን ሁኔታ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ እና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ተንትኖ በጥናት ላይ የተመሰረት ጥናት በማድርግ መሰራት የሚችል እና ሶስት እና ከዚያ በላይ የሰሩበት የተቋማት የሥራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. የሚሰበሰበው መረጃ የዳሞትን የሥራ ክልል መሠረት ተደርጎ በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ መረጃ ማስባሰብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  6. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፓስታ ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለበት፡፡
  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኒ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በራስዎ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 8 የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ እስከ ቀኑ 8፡00 በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይ ሲሆን በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች በተገኙበት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጉልም፡፡
  10. ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፈቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መጠየቅ እና መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here