ለክብረ ወሰን የበቃዉ – ፑምክል

0
30

በጀርመን የዓምስት ዓመት እድሜ ያለው ፈረስ 56 ነጥብ ስድስት ሴንቲ ሜትር በተለካ ቁመቱ በዓለም አቀፍ የድንቃ ድንቅ መዝጋቢ ድርጅት  ለክብረወሰን በቅቶ የምስክር ወረቀት ማግኘቱን ዩፒአይ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት አስነብቧል::

ረጅም ጭራ እና የጋማ ፀጉር የተቸረው “ፑምክል” የተሰኘው ድንክ ፈረስ አሳዳሪ እና ተንከባካቢ ካሮላ ዌይድማን  የተባለች ሴት ስለቁመቱ ማጠር ሰምታ በ2020 እ.አ.አ የአምስት ወር ግልገል ሳለ ቁመቱ 47 ሴንቲ ሜትር እያለ ባለበት ተገኝታ ማየቷን ጠቁማለች::

የፑምክል አሳዳሪ ጓደኛዋ “ለፈውስ” ወይም አስፈግገው ዘና የሚያደርጉ የተለዩ እንስሳትን ያፈላልግ ነበርና ስለድንኩ ፈረስ መስማቱን ሲነግራት ውላ ሳታድር መኖሪያው ድረስ ሄዳ የግል ሀብቷ ማድረግ መቻሏንም ነው የተናገረችው::

በካሮላ ዌይድማን መኖሪያ አራት ዓመት ከመንፈቅ ያስቆጠረው ድንኩ ፈረስ በእርሻ ቦታዋ በመርዳት አብሯት እንደሚዟዟር እና ሙሉ ጤናማ መሆኑን ነው ያስረዳችው:: የቁመቱ ማጠር የተፈጥሮ ልዩ መገለጫው መሆኑን መገንዘቧንና በዝርያ ልዩነት የመጣ አለመሆኑን አስርድታለች ለመዝጋቢዎቹ::

“ፑምክል” በ2020 እ.አ.አ 47 ሴንት ሜትር ወይም አንድ ማስመሪያ ከግማሽ ያክል የነበረው ቁመቱ ድንኩ ፈረስ ከአምስት አመታት ቆይታ በኋላ በ2025 እ.አ.አ አምስት ሴንቲ ሜትር ያህል ብቻ ቁመቱ ጨምሮ  56 ሴንቲሜትር መድረሱን  ልብ ይሏል::

አሳዳሪ ባለንብረቷ ካሮላ ዌይድማን አጭሩ ፈረስ ዘና፣ ፈታ የማድረግ፣ ስሜትን የማነቃቃት “ህክምና” የመስጠት ስልጠና መውሰዱን እና በተለያዩ የየካል ጉደተኞች በሚኙባቸው ተቋማት እየተዟዟረ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግራለች:: ከሚጐበኛቸው ተቋማት መካከልም ሆስፒታሎች፣  የአካል ጉዳተኞች ትምህርት ቤቶች የመሳሰሉት እንደሚገኙበት ነው የድረ ገጹ ጽሁፍ በማጠቃለያነት ለንባብ ያበቃው::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here