ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
20

አቶ መላኩ ኑሬ ፀሐይ በፀደይ ባንክ ዳሞት ቅርንጫፍ የተበደሩትን ብድር በዉሉ መሰረት መመለስ ስላልቻሉ ለብድሩ አመላለስ በመያዣ የተያዘዉን በመያዣ ሰጨዉ በአቶ ሞላ ፀሀይ አፈወርቅ ስም የተመዘገበ በፍኖተ ሰላም ከተማ 02 ቀበሌ በካርታ ቁጥር 9/100/2014 በሰሜን አይሸሽም ሞላ፣ ደቡበ መንገድ በምሥራቅ አበባዉ ጥበቡ፣ ምዕራብ አስማማዉ አስማረ የሚዋሰንና የቦታዉ ስፋት 183.5 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት ህዳር 5/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በመነሻ ዋጋ ግምት ብር 3,636,715 /ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰለሳ ስድስት ሽህ ሰባት መቶ አስራ ምስት ብር/ ይጫረታል፤ በመሆኑም  በእለቱ ተገኝቶ ማንኛዉም ሰዉ መጫረት ይችላል፡፡

  1. ጨረታዉ የሚካሄድበት ቦታ ዳሞት ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ፀደይ ባንክ ዳሞት ቅርንጫፍ ቢሮ ዉስጥ ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋዉን 1/4ተኛው በፀደይ ባንክ ማንኛዉም ቅርንጫፍ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ ማንነታቸዉን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘዉ መቅርብ አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የሚጫረተዉ ሰዉ ዉክልና የምዝገባ ማስረጃ እና የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  5. ለመንግስት የሚከፈል ማንኛዉም ግብር ቫትን ጨምሮ እንዲሁም ከመንግስት የሚጠየቅ የሊዝም ሆነ ከቦታዉና ቤቱ ጋር የተያያዘ ክፍያ እና ከስመ ንብረት ዝዉዉር ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ማናቸዉም ወጭዎች በተጫራቹ (በገዥ) የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊዉ ጨረታዉን ባሸነፈ በ15 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን ሙሉን ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅና ቤቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  7. ገዥዉ በ15 ቀን ዉስጥ ሙሉ ገንዘቡን ገቢ ካላደረገ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታዉ እንደገና ይወጣል፡፡
  8. ባንኩ የተሻለ አመራጭ ካገኘ  በጨረታዉ አይገደድም፡፡

ፀደይ ባንክ ፍኖተ ሰላም ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here