ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
79

በደ/ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን ለ2017 በጀት አመት ለመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የዶዘር ማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ፡-

  1. በየዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200‚000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 50 /አምሳ / ብር በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውላል፡፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸጋል በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች  (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  12. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
  13. ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  14. በማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. የመልካም ሥራ አፈጻጸም መገለጫ እና ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  17. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  18. የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደርያ ሃሳብ ላይ ለወጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  19. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስሥልክ ቁጥር 09 18 28 07 69 ደውሎ መጠየቅ  ይቻላል፡፡

የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here