የባህር ዳር ከተማ የመ/ው/ፍ/አገ/ ድርጅት አንድ ተሸከርካሪ ሾፌር እና ነዳጅ አከራይ ሸፍኖ ድርጅቶችን (ግለሰቦችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ1አመት ለዋናው መስሪያ ቤት እና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ሰርቢስ መከራየት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለኪራይ የቀረበውን ተሸከርካሪ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በየወሩ የአገልግሎት ክፍያው ሲፈፀም ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 20,000 (ሃያ ሽህ) ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚንቀሳቀሱበት ፌርማታ (ቦታዎች) ቀበሌ 08 ከዋናው የውሃ አገ/ድርጅት ተነስቶ በጊወርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ ቀበሌ 13 አየር መንገድ ዘጌ መገንጠያ ወደ ሄደበት ተመልሶ ማድለቢያ፣ገጠር መንገድ ይዞ በቀበሌ 16 ቁልቋል ትምህርት ቤት ቻይና ካምፕ ወደ ቀበሌ 14 አቡነሀራ ገበያ ወደ ልደታ ቤተ ክርስቲያን አስፋልት ወደ ዱዱ 40 ሜትር መስቀለኛ ወደ ባታ ቤተክርስቲያን ደርሶ በሄደበት ተመልሶ ልደታ ታክሲ ተራ ወደ ቀበሌ 14 ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወደ አኮቴት አደባባይ አዲናስ ሆስፒታል ወደ አዝዋ ሆቴል አስፋልት ቀጥታ በፓፒረስ ዋናው ቢሮ መነሻ ቦታ መድረስ ሲሆን በአጠቃላይ ከአባይ ወንዝ ምዕራብ ያለውን አካባቢ ጥዋትና ማታ ሰርቢስ የመስጠት፡፡
- ሞዴላቸው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2014 እና በላይ ያለና የወንበር ልብሱ የተሻለ መኪና ለድርጅታችን ለማከራየት የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ) ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 222 ገዝቶ በመውሰድ መጫረት ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የዋጋ ማወዳደሪያ ፖስታዎችን በማሸግ በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 202 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል ::
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15 ተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ባህር ዳር በስልክ ቁጥር 058 320 70 59 መጠቀም ይቻላል፡፡
የባህር ዳር ከተማ የመ/ው/ፍ/አገ/ ድርጅት

