በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሊቦ ከምከም ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2 የመኪና ጎማ እና ሎት 3 የብዙሀን መገናኛ እቃዎች ከተጫራቾች መካከል በማወዳደር በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዱን ያደሱ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሊቦ ከም/ወ/ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1 ብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ ሎት 2 የመኪና ጎማ ብር 22,000 /ሃያ ሁለት ሽህ ብር/ ብቻ እና ሎት 3 የመገናኛ ብዙህን እቃዎች ብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ መቁረጥ እና ከሰነዱ ጋር ኮፒ መያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት እስከ 11፡30 ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁ 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተዘጋጀው ሳጥን እስከ 15 ተኛው ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ15 ተኛው ቀን 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን በ16 ተኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ 16 ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ ግዥ ላይ 20 በመቶ ከፍና ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው አካል የሚለየው በጥቅል ነው፡፡
- አሸናፊው አካል ያሸነፈውን እቃ ሊቦከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማድረስ አለበት፡፡
- ጨረታውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖርው እና እንዲነበብ ተድረጎ መሙላት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ሁሉም ሎቶች በተጠየቁት ጥራት (ስፔስፊኬሽን) መሰረት በባለሙያ ተፈተሾ ማሰረከብ የሚችል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኙት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 01 95 /931 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

